በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ ድል ተጎናጸፉ


የኒውዚላንዱዋ ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደርን ዛሬ በመላ ሃገሪቱ በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ አሸንፈዋል።

ሁለት ሶስተኛው የህዝብ ድምጽ ተቆጥሮ የጠቅላይ ሚኒስትሩዋ ሌበር ፓርቲ ከወዲሁ አርባ ዘጠን ከመቶውን ድምጽ እንዳገኘ ተዘግቧል፥ ፓርቲያቸው ከፓርላማው አንድ መቶ ሃያ መቀመጫዎች ስድሳ አራቱን ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል።

እስካሁን በተቆጠረው የጠቅላይ ሚኒስትሩዋ ፓርቲ ያገኘው ድምጽ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ተፎካካሪያቸው ጁዲት ኮሊንስ ከወዲሁ መሸነፋቸውን ተቀብለው ቴለፎን ደውለው እንኩዋን ደስ ያለዎ ብለዋቸዋል።

የጁዲት ኮሊንስ ወግ አጥባቂ ብሄራዊ ፓርቲ ሰላሳ አምስት የምክር ቤት መቀመጫ ያገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህ ያሁኑ ለፓርቲው በሃያ ዓመታት ውስጥ ባልታየ መልኩ ዝቅተኛ የሆነ ክንዋኔ እንደሆነ ተነግሯል።

ጃሲንዳ አርደርን ያገኙት ድምጽ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ፓርቲያቸው ሌበር እ አ አ ከ 1946 ወዲህ አግኝቶት የማያውቀውን ጥንካሬ ያጎናጸፈዋል ተብሎ ተጠብቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምላሻቸው ከፍተኛ እድናቆት አትርፈዋል፤ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ባላት በሀገሪቱ በኮቪድ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉት ሃያ አምስት ሰዎች ብቻ ናቸው።

ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ባለፈው ዓመት የነጭ የበላይነት አቀንቃኝ ታጣቂ በመስጊዶች ላይ ጥቃት ከፍቶ ሃምሳ አንድ ሰዎች በገደለበት ጊዜ ያሳዩት ርህራሄ እና በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ረገድ የወሰዱት ወሳኝ ርምጃ ተወዳጅነት አትርፎእቸዋል።

XS
SM
MD
LG