በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ሥርጭት እየጨመረ ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የኮሮናቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ነው። በበሽታው ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር ከሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ አልፏል።

ኒው ዮርክ ከተማ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ከዛሬ ጀምረው ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቃለች።

የከተማዋ ባለሥልጣናት ከዚህ ውሳኔ የደረሱት በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ለሰባተኛ ተከታታይ ቀን ከሦስት ከመቶ ካለፈ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

ቦስተን እና ዲትሮይትን ጨምሮ ሌሎች ትላልቅ ከተሞችም ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል።

በአሁኑ ጊዜ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ያሉት የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከአስራ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን አልፏል። ሆስፒታል የሚገቡት ህሙማን ቁጥርም እጅግ እየጨመረ በመሆኑ የጤና ሰራተኞች ላይ ጫና አሳድሯል።

በርካታ የሃገሪቱ ክፍለ ግዛቶች ቀደም ብለው ተነስተው የነበሩትን የእንቅስቃሴ ገደቦች መልሰው እያጸኑ ናቸው።

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ከሩቅም ከቅርብም የሚያሰባስበው መጪው የምስጋና ቀን በዓልም ባለሥልጣናትን አብዝቶ ስጋት ላይ ጥሏል።

የቨርጂኒያ ሃገረ ገዢ ራልፎ ኖርታም ቤተሰቦች በዓሉን በየቤታቸው እንዲያሳልፉ ተማጽነዋል፥ ይህን የምናደርገው ለቤተሰቦቻችን ካለን ፍቅር አኳያ ነው ሲሉም አሳስበዋል።

በሌላም በኩል በሚገባ የሚሰራ እና የጎን የጤና ጠንቅ የማያስከትል የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ማግኘቱ ጥረት ዛሬም አዲስ መልካም ዜና ይዞ መጥቷል።

ላንሴት በተባለው ስመ ጥር የህክምና መጽሄት ላይ የወጣ አዲስ ሪፖርት እንዳለው የብሪታንያው አስታር ዜኔካ ኩባኒያ ከኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲ ጋር የቀመመው ክትባት በሙከራው በተሳተፉ ወጣቶችም በዕድሜ የገፉ ሰውችም ላይ ጠንካራ የሰውነት የቫይረሱ መከላከያ እንደፈጠረ እና የጎን የጤና ጠንቅም እንዳልታየባቸው አመልክቷል።

ቀደም ብሎ የዩናያትድ ስቴትስ የመድሃኒት ኩባኒያ ፋይዘር ከጀርመኑ ባዮንቲክ ጋር የሰሩት እንዲሆም ሌላው የአሜርካ ኩባኒያ ሞዴርና የሰራው ክትባት አመርቂ ውጤት እንዳስገኙ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

XS
SM
MD
LG