በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አትሌት ግርማይ ገ/ሥላሴ የኒውዮርክ ማራቶንን አሸነፈ


ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረሥላሴ
ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረሥላሴ

ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረሥላሴ የኒውዮርክ ማራቶን አሸነፈ፡፡

በዓለምአቀፍ መድረክ 2ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሩ ያስገኘው ግርማይ ገ/ሥላሴ ዛሬ የተካሄደውን የኒውዮርክ ማራቶን ያጠናቀቀው 2 ሰዓት ከ07 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ነው፡፡

ኬኒያዊቷ አትሌት ሜሪ ኬታኒ
ኬኒያዊቷ አትሌት ሜሪ ኬታኒ

ኬኒያዊው አትሌት ሉቃስ ሮቲች 2ኛ አሜረካዊው አብዲ አብዲረሃማን 3ኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡

በሴቶች ኬኒያዊቷ ሜሪ ኬታኒ 1ኛ ስትሆን የሃገሯ ልጅ ሳሊ ኪፕዮጎ እና አሜሪካዊቱ ሞሊ ሀድል 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ አሰለፈች መርጊያና አያንቱ ደቀቦ ስድሥተኛና አሥረኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡

XS
SM
MD
LG