በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የጤና ድርጅት ለወረርሽኞች የተፋጠነ ምላሽ ለመስጠት ሥምምነት ላይ ደረሰ


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ህንፃ ላይ ተቀምጦ የሚታየው የዓለም የጤና ድርጅት አርማ፤ ጄኔቫ
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ህንፃ ላይ ተቀምጦ የሚታየው የዓለም የጤና ድርጅት አርማ፤ ጄኔቫ

የዓለም የጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እንደ ኮቪድ-19 ያሉ አጣዳፊ የጤና ሥጋቶች ሲከሰቱ ሲቀሰቀሱ ድርጅቱ ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲችል የሚረዳው አዲስ ኮሚቴ መሰረተ። የተመዱ የጤና ተቋም በዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አያያዙ መነቀፉ ይታወቃል።

መንግሥታት እና የዓለሙ የጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲጀምር የተፈጸሙ ስህተቶችን እንደመንኪፖክስ ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ በመሳሰሉ ሌሎች ወረርሽኞች መድገም የለባቸውም በማለት አንዳንድ የበሽታዎች ኤክስፐርቶች ያሳስባሉ።

የአጣዳፊ የጤና ሥጋት መከላከል፣ ዝግጁነት እና ምላሽ ሰጪ ቋሚ ኮሚቴ እንዲመሰረት ሠላሳ አራቱም የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፈዋል።

XS
SM
MD
LG