በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ድምፅ አዲስ ዳይሬክተር ተሾመለት


የቀድሞ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ እና የፍሪደም ሃውስ ፕሬዚዳንት ማይክል አብራሞዊትዝ
የቀድሞ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ እና የፍሪደም ሃውስ ፕሬዚዳንት ማይክል አብራሞዊትዝ

የቀድሞ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ እና የፍሪደም ሃውስ ፕሬዚዳንት ማይክል አብራሞዊትዝ አዲሱ የአሜሪካ ድምጽ ዳይሬክተር ኾነው ተሾሙ።

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ሚዲያ /ዩ ኤስ ኤ ጂ ኤም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አማንዳ ቤኔት፣ ፍሪደም ሃውስ የተባለው የምርምር ተቋም በፕሬዚዳንትነት በማገልገል ላይ የሚገኙት፣ የቀድሞው ጋዜጠኛ ማይክል አብራሞዊትዝ በሚቀጥሉት ወራት አዲሱን ሥራቸውን እንደሚጀምሩ ዛሬ ለአሜሪካ ድምጽ ሠራተኞች በኢሜል በላኩት መልዕክት አስታውቀዋል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2017 ዓ.ም ጀምረው የፍሪደም ሃውስ ፕሬዚደንት የሆኑት አብራሞዊትዝ የሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ሲኾኑ ሥራ በጀመሩበት ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ለ24 ዓመታት ሠርተዋል።

በተጨማሪም የአይሁዶች ጭፍጨፋ ሰለባዎች መታሰቢያ ቤተ መዘክር "ሆሎኮስት ሚዩዚየም" ለስምንት ዓመታት የዘር ማጥፋትን መከላከል እና በአይሁዶች ላይ ስለተፈጸመው ፍጅት ማስተማር ላይ ያተኮረ ሥራ ሠርተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG