በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሥራ ዘጠነኛው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጉባዔ

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ

ከጊዜ ወደጊዜ ሥልጣናቸው እየፈረጠመ የሄደው የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ኮሙኒስት ፓርቲው ሕዝብ ለሚያቀርባቸው ጥያቂዎች ዲሞክራሲና ፍትህ እንዲሰፍን ለሚደረጉ ጥሪዎች በተሻለ ምላሽ እንዲሰጥ አደርጋለሁ ሲሉ ቃል ገቡ።

ከጊዜ ወደጊዜ ሥልጣናቸው እየፈረጠመ የሄደው የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ኮሙኒስት ፓርቲው ሕዝብ ለሚያቀርባቸው ጥያቂዎች ዲሞክራሲና ፍትህ እንዲሰፍን ለሚደረጉ ጥሪዎች በተሻለ ምላሽ እንዲሰጥ አደርጋለሁ ሲሉ ቃል ገቡ።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ቃል የገቡት በአሥራ ዘጠነኛው የፓርቲው ኮንግሬስ ጉባዔ ላይ ባሰሙት ረጅም ንግግር ነው።

ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት በጥበቆች ላይ በተፈፀመው የማዋከብ ተግባርና የኢንተርኔት ጥቃት አኳያ ሲታይ ፕሬዚዳንቱ የገቡትን ቃል እንዴት ተግባራዊ ሊያደርጉት ነው የሚለውን ከባድ ጥያቄ አስነስቷል።

ይህ በዚህ እንዳለ ፕሬዝዳንት ሺ ዥን ፒንግ ሀገራቸው የዓለም ልማት ተሳታፊ ሆና እንደምትቀጥል አስታወቁ።

አስቀድማ ቻይና በሀር ንግድ መስመር አውሮፓና አፍሪካ ጋር የነበራትን ግንኙነት እንደገና በማሰብ

“አንድ መንገድ አንድ መቀነት” የሚል መመሪያ ቀርፃለች። በዚህ የንግድ ትሥሥር መንገድ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚፈስም ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG