በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታይላንድ ዋሻ ውስጥ ጠፍተው የተገኙ ታዳጊዎች ለማውጣት ጥረት እየተደረገ ነው


ጎርፍ ካጥለቀለቀው ዋሻ መውጫ ካጡ ሁለት ሳምንት ገደማ የሆናቸውን የታይላንድ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በህይውት ለማውጣት የሚቻልበት መንገድ እየተፈለገ ነው።

ጎርፍ ካጥለቀለቀው ዋሻ መውጫ ካጡ ሁለት ሳምንት ገደማ የሆናቸውን የታይላንድ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በህይውት ለማውጣት የሚቻልበት መንገድ እየተፈለገ ነው።

የታይላንድ የባህር ኃይል ባወጣው አዲስ ቪዲዮ ኳስ ተጫዋቾቹ በዚህ ሳምንት የደረሱላቸው ባህር ጠላቂዎች ያደረሱላቸውን ከስስ አሉሚኑም የተሰሩ ብርድ ልብሶች ለብሰው ይታያሉ። ስማቸውን ደኅንነታቸውን ሲናገሩም ይታያሉ። አሥራ ሁለቱ ታዳጊ ወንዶች ልጆችና አሰልጣኛቸው በተሸጎጡበት በዋሻዎቹ ጥልቅ ጉድባ ውስጥ ቁልጭ ቁልጭ ሲሉ የተገኙት ሰኞ ዕለት ነው።

የታይላንድ የአገር አስተዳደር ሚኒስትር ሲናገሩ ልጆቹ ጥልቅ ውሃ ዋና ዘዴ መሰልጠን ይኖርባቸው ይሆናል ነገር ግን አንዳንዶቹ ፈጽሞ መዋኘት ስለማይችሉ አዳጋች ሊሆን ይችላል ብለዋል። የጥልቅ ውሃ መዋኛ መሳሪያ ተልኮ በአፋጣኝ ካልወጡ የውሃው ከፍታ ከጨመረ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG