ዋሺንግተን ዲሲ —
ከአንድ ወር በላይ በፊት ‘Idai’ የተባለ ሳይክሎን ከፊል ደቡብ ምሥራቅ አፍሪካ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ አይዘነጋም።
የፈረንሳይ የአየር ትንበያ አገልግሎት ‘Tropical Cyclone Kenneth’ የሚለው ማዕበል ዛሬ ከማዳጋስካር በስተሰሜን በኩል 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደርሶ ወደ ኮሞሮስ ደሴት እያመራ እንደሆነ ተገልጿል።
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር የጣምራ ታይፉን ማስጠንቀቅያ ማዕከል በገለፀው መሰረት እስከዛሬ ሌሊት ባለው ጊዜ ውስጥ የትሮፒካል የማዕከል ነፋስ በሰዓት 90 ኪሎሜትር ይነፍሳል። በሰዓት እስከ 120 ኪሎሜትር ሊሄድ ይችላል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ