በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻድ ምክር ቤር የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን ዘመን ለማራዘም ሕገ ሊያወጣ ነው

ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ
ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ

የቻድ ምክር ቤት በያዝነው ሳምንት የፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢን የሥልጣን ጊዜ ሊያራዝም የሚችል አዲስ ህገ መንግሥት ለማውጣት ተስማምቷል። ፕሬዚዳንቱ እአአ ከ1990 አንስቶ ለ28 ዓመታት ሀገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል። እአአ ከ2005 ጀመሮ ደግሞ በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል።

የቻድ ምክር ቤት በያዝነው ሳምንት የፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢን የሥልጣን ጊዜ ሊያራዝም የሚችል አዲስ ህገ መንግሥት ለማውጣት ተስማምቷል። ፕሬዚዳንቱ እአአ ከ1990 አንስቶ ለ28 ዓመታት ሀገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል። እአአ ከ2005 ጀመሮ ደግሞ በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል።

እአአ ግንቦት 17 ቀን የቡሩንዲ ህዝብ ፕሬዚዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ለተጨማሪ 16 ዓመታት በሥልጣን እንዲቆዩ በሚያስችል የህገ መንግሥት ማሻሸያ ላይ ድምፅ ይሰጣል።

በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ የፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ የሥልጣን ጊዜ ወደ 18 ወራት ከሚጠጋ ጊዜ በፊት ያበቃ ቢሆንም ሥልጣን አልለቅም በማለታቸው የሰብዓዊው ቀውስ ሁኔታ እየተባባሰ ሄዷል።

የፕሬዚዳንቶች ሥልጣን የጊዜ ገደብ በአፍሪካ ሀገሮች ዙርያ መሰረቱን እየለቀቀ ይመስላል። የአፍሪካ ስትራቴጃዊ ጥናት ማዕከል በያዝነው ዓመት ያወጣው ጥናት የፕሬዚዳንቶችን የጊዜ ገደብ የሚወስነውን ህገ መንግሥት በተግባር ላይ ያዋሉት ሀገሮች ከአርባ ከመቶ ያነሱ መሆናቸውን አሳይቷል። ከሁለት ጊዜ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን በኋላ የወረዱት የ15 ሀገሮች መሪዎች ብቻ መሆናቸውን ጥናቱ ጠቅሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG