በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ ያሉ ታቀዋሚዎች አዲሱ ፕሬዚዳንት ያደረጉትን ንግግር ነቀፉ

አዲሱ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ
አዲሱ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ

በደቡብ አፍሪካ ያሉ ታቀዋሚዎች አዲሱ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ ያደረጉትን የመጀመርያ ንግግር አጥብቀው ነቅፈዋል። አዲሱ ፕሬዚዳንት በሀገሪቱ ያሉትን በርካታ ተግዳሮቶችን የሚመለከት ተጨባጭ ዕቅድ ይኖራቸው እንደሆነ ተጠራጥረዋል።

በደቡብ አፍሪካ ያሉ ታቀዋሚዎች አዲሱ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ ያደረጉትን የመጀመርያ ንግግር አጥብቀው ነቅፈዋል። አዲሱ ፕሬዚዳንት በሀገሪቱ ያሉትን በርካታ ተግዳሮቶችን የሚመለከት ተጨባጭ ዕቅድ ይኖራቸው እንደሆነ ተጠራጥረዋል።

ራማፎሳ ተወዳጅነት ያልነብራቸውን ጃኮብ ዙማን በተኩ ማግስት ባለፈው አርብ ባደረጉት ንግግር ሰፊ ዕቅድ አቅርበዋል። ደቡብ አፍሪካውያን የታላቁን መሪያቸው ፈለግ እንዲከተሉም መክረዋል።

በህብረት ሆነን በሀገራችን ታሪክ እንሰራለን ሲሉ በአብዛኛው መልካም አቀባበል ላደረገላቸው ምክር ቤት ተናግረዋል። ለሀገራችን ባለን ፍቅር ተሳስረን ባለፈው ያደረግነውን አሁንም እንደግመዋልን። የተደቀኑብንን ተግዳሮቶች ቆርጠን በመነሳት እንወጣቸዋለን። አብረን በመስራትም ኔልሰን ማንዴላ ህይወታቸውን ሙሉ የጣሩበትን ፍትኃዊና ጽኑ ማኅበረሰብ እንገነባለን ሲሉ ራማፎሳ ተናግረዋል።

ከዚያ በኋላ አርባ የሚሆኑ የገዢው ፓርት የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ አባላትና ተቃዋሚውዎች ተከራክረውበታል።

ራማፎሳ ባደረጉት ንግግር ያቀረቡት ከትምህርት እስከ ጤና ጥበቃ የሚሄድ ዕቅድ እያንዳንዱ ተብጠልጥሎ ጥያቄ ቀርቦበታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG