በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜክስኮ ድንበር የሚመጡ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ሂደት የሚያሳጥር አሰራር ወጣ


ፎቶ ፋይል፦ ከሜክሲኮ ድንበር አቋርጠው በዩማ፣ አሪዞና የደረሱ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞች በአሜሪካ የድንበር ጠባቂዎች እየተስተናገዱ እአአ ጥር 22/2022
ፎቶ ፋይል፦ ከሜክሲኮ ድንበር አቋርጠው በዩማ፣ አሪዞና የደረሱ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞች በአሜሪካ የድንበር ጠባቂዎች እየተስተናገዱ እአአ ጥር 22/2022

የባይደን አስተዳደር በሜክሲኮ ድንበር በኩል የሚመጡ የጥገኝነት (አሳይለም) ጠያቂዎችን አቤቱታ ለመወሰን ዓመታት የፈጀውን ጊዜ ቢያንስ በወራት ለማሳጠር የሚረዳ የአሰራር ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ፡፡

አዲሱ ደንብ የኤምግሬሽን ሰራተኞች በሜክሲኮ በድንበር በኩል የሚመጡትን የጥገኘት ጥያቄዎችን የኤምግሬሽን ዳኞች መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው እዚያ ቶሎ በማየት የሚያጸድቁበትን ወይም ውድቅ የሚያደርጉበት ሥልጣን ሊሰጣቸው እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

የኤምግሬግሽን ፍርድ ቤቶች ወደ 1.7 ሚሊዮን በሚጠጉ አመልካቾች ውዝፍ ፋይል የተጨናነቁ መሆናቸው ሲነገር አሁን ባለው አሰራር አንድን የጥገኘነት ጉዳይ ተመልክቶ ለመወሰን በአማካይ እስከ አራት ዓመት ጊዜ የሚወስድባቸው መሆኑን ተነገሯል፡፡

አዲሱ ደንብ በሁለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG