ኮቪድ-19 ኢንሱሊን የሚያመነጨውን የሰውነት ክፍል በመጉዳት አንዳንድ ህሙማንን ለስኳር ህመም ይበልጥ የተጋለጡ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡
ጣሊያን ውስጥ በሲኤና ዩኒቨርስቲ ምርምር ያደረጉት ሳይንቲስቶች ግኝት ቫይረሱ ኢንሱሊን የሚያመነጩ የጣፊያ ህዋሳትን እንደሚያጠቃ ገልጸዋል፡፡
ኒው ዮርክ ዊይል ኮርኔል ሜድስን ውስጥ የተደረገ ሌላ ጥናት ደግሞ ኮቪድ-19 የሰውነት የጎሎኮስ መጠንን የሚቆጣጠረውን ሆርሞን በመጉዳት በቂ ኢንሱሊን እንዳያመነጭ የሚያደረግ መሆኑን አመልክቷል፡፡
የክትባት ግዴታውን ያልተወጡ የጤናው ዘርፍ ሠራተኞ ተባረሩ
በደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የምትገኘው የኖርዝ ካሮላይና ግዛት መንግሥት ያወጣውን የክትባት ግዴታ ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነው ያልተገኙ የጤና ሠራተኞችን ማባረሩን አስታውቋል፡፡
በኖርዝ ካሮላይና ከሚገኙ 15 ሆስፒታሎችና 800 ክሊኒኮች ውስጥ ይሠሩ ከነበሩት መካከል የተቀመጠውን መመሪያ ባለማክበራቸው 175 የሚሆኑ ሠራተኞች ከሥራ መባረራቸው ተገልጿል፡፡
የኒው ዮርክ ባለሥልጣናት ለጤናው ዘርፍ ሰራተኞች ያወጡት የክትባት ግዴታ መርሃ ግብር ውጤታማ መሆኑን አስታወቁ፡፡
የኒው ዮርክ ገዥ ካቲ ሆቹሉ ጽ/ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ በኒው ዮርክ ከሚገኙት 650ሺ የሆስፒታልና የጤና እንክብካቤ መስጫ ተቋማት ሠራተኞች ውስጥ 92 ከመቶ የሚሆኑት ቢያንስ አንደኛውን ዙር ክትባት ባላፈው ሰኞ ከተቀመጠላቸው የግዴታ ቀነ ገደብ በፊት መውስዳቸውን አስታውቋል፡፡