በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልጆቻቸው የተገደሉባቸው ወላጆች በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የይቅርታ መልዕክት ዙሪያ

ፎቶ ፋይል፡ በመስከረም ወር 2009 ዓ.ም በኢሬቻ በዓል ላይ የነበሩ ተሳታፊዎች ከገቡበት ገደል ለመውጣት ሲጣጣሩ
ፎቶ ፋይል፡ በመስከረም ወር 2009 ዓ.ም በኢሬቻ በዓል ላይ የነበሩ ተሳታፊዎች ከገቡበት ገደል ለመውጣት ሲጣጣሩ

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በፓርላማ ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ሕወታቸው ለተቀጠፈ ሰዎች መፀፀታቸውን ገልፀው ይቅርታ ጠይቀዋል። በቅርቡ ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው መካከልይቅርታ ብቻውን ለደማ ልብ መጠገኛ ሊሆን አይችልም ይቅርታው ተቀባይነት የሚኖረው ድርጊቱን የፈፀሙ ሰዎች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው ብለዋል።

ልጆቻቸው የተገደሉባቸው ወላጆች በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የይቅርታ መልዕክት ዙሪያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:06 0:00

"የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ" ሲሉ ከዚህ ቀደም በደንቢዶ ዶሎ ከተማ ስለተገደለ የ16 ዓመት ኃይሉ ኤፍሬም አሟሟት የተናገሩት እናንት ወይዘሮ ታደሉ ተማምን ስለ ዶ/ር አብይ የይቅርታ መልዕክት ተጠይቀው “እኔ ሁሉም ነገር የተደበላለቀብኝ ሰው ነኝ የምናገረው የለኝም።” ብለዋል።

"የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ" ሲሉ ከዚህ ቀደም በደንቢዶ ዶሎ ከተማ ስለተገደለ የ16 ዓመት ኃይሉ ኤፍሬም አሟሟት የተናገሩት እናንት ወይዘሮ ታደሉ ተማምን ስለ ዶ/ር አብይ የይቅርታ መልዕክት ተጠይቀው “እኔ ሁሉም ነገር የተደበላለቀብኝ ሰው ነኝ የምናገረው የለኝም።” ብለዋል።

በመርሳ ከተማ በሐብሩ ወረዳ የተገደለው የ23 ዓመቱ ወጣት አብዱ ሞላ ወላጅ አባት አቶ ሞላ ንጋቱ፣ በነቀምት ከተማ የተገደለ የ13 ኦኣመት ወጣት አብሳ እንዳለ አባት አቶ እንዳለ ፉፋ እንዲሁም በወልዲያ ከተማ የተገደለው የ35 ዓመቱ ገብረመስቀል ጌታቸው አባት አቶ ጌታቸው ኃይሌ ስለ ዶ/ር አብይ ይቅርታ ተጠይቀዋል።

የሰጡትን ምላሽ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG