አዲስ አበባ —
የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው አሰፋን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከትግራይ ክልል ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ እንዳስታወቀው፣ መቀሌ የሚገኙት አቶ ጌታቸው በፖሊስ እንደሚፈለጉ ከታወቀ ቆይቷል፤ የእሥር ማዘዣም ከወጣባቸው ቆይቷል፡፡
አቶ ጌታቸው አሰፋ የተጠረጠሩት በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ነው፡፡
በሌላም በኩል ሰሞኑን የሚከበረውን የገናን በዐል ምክንያት በማድገር ከ5መቶ በላይ ለሚሆኑ ታሣሪዎች ይቅርታ መደረጉን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ