በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዝናብ አዘል አውሎ ንፋስ/ማዕበል/ የተመቱት የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች


ኒው ኦርሊንስን ከተማ
ኒው ኦርሊንስን ከተማ

"አካባቢውን ለቃችሁ ሄዳችሁ ከሆነ ከየአጥቢያችሁ አብያተክርስትያናት ተጠሪ ካልሰማችሁ አሁን የመመለሻው ጊዜ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። የንግድ ቤቶች አልተከፈቱም። የገበያ መደብሮች፤ ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው። እውነቱን ለመናገር የውሃ እና የመብራት አቅርቦቶች ላይ ጫና ላለማሳደር መጣር አለብን። ስለሆነም ወደየቀያችሁ ከመመለሳችሁ በፊት እባካችሁ የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ጽ/ቤትን ምክር ጠይቁ ወይም በየአጥቢያ አብያተክርስትያን በኩል የሚተላለፈውን መመሪያ ተከታተሉ።"

በደቡብ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትሷ የሉሲያና ክፍለ ግዛት ሄሬከን አይዳ የሚል ሥያሜ በተሰጠው ከባድ ዝናም የቀላቀለ (ማዕበል የሚያስከትል) አደገኛ አውሎ ነፋስ ባመጣው ጎርፍ የተጠመዱ ሰዎችን ለማትረፍ የነብስ አድን ሰራተኞች ጀምረውት የነበረውን ሥራ ዛሬ ይጀምራሉ።

አገረ ገዥው ሄሬከን አይዳ ከመድረሱ አስቀድሞ አካባቢውን ለቀው የሄዱ ሰዎች ወደ ቀያቸው የመመለሻቸውን ጊዜ እንዲያዘገዩ ያሳሰቡበትን መግለጫ ተከትሎ ወታደራዊና የሲቪል ጀልባዎች ለነብስ አድን ሥራ በጎርፍ የተጥለቀለቀውን አካባቢ ማሰስ ይዘዋል።

በጭለማ የተዋጠችውን የኒው ኦርሊንስን ከተማ ጨምሮ የውሃና የመብራት አገልግሎቶች ለተቋረጡበት ቁጥሩ አንድ ሚልዮን ለሚደርሰው የሉዊዝያና እና የሚሲሲፒ ክፍለ ግዛቶች ነዋሪዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር በሚያስፈልገው ሥራ ለማገዝ ከተለያዩ ክፍለ ግዛቶች የመጡ የጥገና ባለሞያዎች ወደ አካባቢዎቹ በመግባት ላይ ናቸው።

ኒውኦርሊንስን ከመሰል አደጋ ለመከላከል ከአስራ ስድስት ዓመት በፊት የካትሪና ማዕበል አካባቢውን አጥለቅልቆ እጅግ የከፋ አደጋ ማድረሱን ተከትሎ የፌዴራል መንግስት በርካታ ቢልዮን ዶላር ወጪ አድርጎ ተጠናክረው እንዲገነቡ ያደረጋቸው የጎርፍ መከላከያ ግድግዳዎች፤ የወንዝ ውሃ ሙሌትን ለመከላከል የተሠሩ መዋቅሮች እና ጎርፍ በመጣ ጊዜ እየተዘጉና እየተከፈቱ የሚሰሩ የግድብ አጥሮች በብቃት በመመገት የመጀመሪያው ተደርጎ የተወሰደውን ከባድ ፈተና ማለፋቸው አረጋግጠዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በዝናብ አዘል አውሎ ንፋስ/ማዕበል/ የተመቱት የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:13 0:00


XS
SM
MD
LG