በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌስቡክ ስሙን የመቀየር ዝግጅቱ ነቀፋ አስነሳበት


ፌስቡክ ስሙን ሊቀይር ዕቅድ አለው የሚል ሪፖርት ትናንት ከወጣ በኋላ የማኅበራዊ መገናኛው ኩባኒያ ላይ ወዲያውኑ ነቀፋ እየቀረበበት ነው።

ሪፖርቱን ያወጣው "ዘ ቨርጅ" የተባለው የኢንተርኔት የዜና አውታር ሲሆን ፌስቡክ ዜናውን ለማረጋገጥ ፈቃደኛ አልሆነም።

ነቃፊዎች በበኩላቸው ፌስቡክ ስሙን ለመቀየር ያቀደው በቅርብ ጊዜያት የተጠመደባቸው ቀውሶች እና ውዝግቦች የሳቡትን ትኩረት ዞር ለማድረግ አልሞ ሊሆን ይችላል ብለውታል።

“ዘ ቨርጅ” ባወጣው ሪፖርት ውጥረት ላይ ያለው ፌስቡክ ራሱን በማህበራዊ መገናኛነት ብቻ የማይወሰን መሆኑን ለማንጸባረቅ ተነስቷል ብሎታል።

እውነተኛውን የፊስቡክን ማንነት ተከታታይ ሲል ራሱን የሚጠራ ቡድን ተሟጋቾች በበኩላቸው ካሁን ቀደም "የነዳጅ እና የትንባሆ ኩባኒያዎች ትኩረት ዞር እንዲልላቸው ስማቸውን ቀይረዋል" ሲሉ አስታውሰዋል። የፊስቡክ ቃል አቀባይ አንዲ ስቶን በጉዳዩ ላይ የምንሰጠው አስተያየት የለንም። ለሪፖርቱ ማረጋገጫም አንሰጥም" ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG