በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ አዲሶቹ የም/ቤት አባላት ቃለ መሃላ ፈጸሙ


ሁለት መቶ ዘጠና የሚሆኑት አዲሶች ተመራጮች ትናንት ሀሙስ ሞቃዲሾ ውስጥ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። በሞቃዲሾ ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግለት አውሮፕላን ማረፊያ እአአ ሚያዚያ 14/2022
ሁለት መቶ ዘጠና የሚሆኑት አዲሶች ተመራጮች ትናንት ሀሙስ ሞቃዲሾ ውስጥ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። በሞቃዲሾ ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግለት አውሮፕላን ማረፊያ እአአ ሚያዚያ 14/2022

ሁለት መቶ ዘጠና የሚሆኑት አዲሶች ተመራጮች ትናንት ሀሙስ ሞቃዲሾ ውስጥ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። የምክር ቤት አባላት ምርጫው በተደጋጋሚ ሲዘገይ በቆየው ምርጫ የተመረጡት ሲሆን የፕሬዚዳንቱ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጸብ በቀጠለበት በዚህ ወቅት ሥነ ስርዓቱ በመዲናዋ አውሮፕላን ማረፊያ ግቢ በጥብቅ የጸጥታ ጥበቃ ተከናውኗል።

የምርጫ ኮምሽኑ ሊቀ መንበር ሙሴ ጌሌ ዩሱፍ ዕለቱን "በሀገራችን የምርጫ ሂደት ታላቅ እርምጃ የተመዘገበበት" ሲሉ አድንቀዋል። ሁለት ዓመት ገደማ የወሰደው ረጅም እና አድካሚ የምርጫ ሂደት የተጠናቀቀበት ታሪካዊ ክንዋኔ ብለውታል።

የጁባላንድ እና ሂርሼቤሌ ክፍለ ግዛቶች ሃያ አምስት መቀመጫዎች ገና እንዳልተያዙም አክለዋል።

የምክር ቤት አባላቱ አፈ ጉባኤ እስከሚመርጡ ድረስ በአዲሱ ፓርላማ ከሁሉም በእድሜ አንጋፋ የሆኑት ሊቀ መንበር ሆነው ያገለግላሉ። ነገ አዲሶቹ አባላት አፈ ጉባኤ እና ከዚያም ፕሬዚደንት ለመምረጥ ዝግጅት ይጀምራሉ።

የሶማሊያ የታችኛው እና የላይኛው ምክር ቤቶች ምርጫ ሊከናወን ታቅዶ የነበረው የፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ የስልጣን ዘመን እአአ ባለፈው 2021 የካቲት ወር ከማብቃቱ አስቀድሞ ነበር። ሆኖም በክልሎችም በአገር አቀፍ ደረጃ ባሉት የፖለቲካ እና የምርጫ ጉዳይ ጭቅጭቆች የተነሳ ሲጓተት ቆይቷል። አዲሱ ፓርላማ በመሰየሙ የሶማሊያ ፖለቲካ ተንታኞች ጥቂት እፎይታ አግኝተዋል።

ሶማሊያዊው ዲፕሎማት ሻፊክ ዩሱፍ ኦመር ለቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል በሰጡት ቃል "በአመዛኙ በፕሬዚደንት መሃመድ አብዱላሂና በጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ንትርክ ምክንያት የምርጫው ሂደት ለረጅም ጊዜ ዘግይቷል። አሁን ምክር ቤቱ መስየሙ ለሀገራችን ፖለቲካ አዲስ ምዕራፍ ያበስራል" ብለዋል።

የምርጫው ሂደት ተጠናቅቆ አዲስ ፕሬዚደንት እንዲመረጥ በዐለም አቅፍ ማህበረሰብ ለወራት የበረታ ግፊት ሲደረግ ቆይቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማሊያ የብዙ ብሊዮን ዶላር ስትረዳ የቆየች ሲሆን የሶማሊያ መንግሥት ከጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን ከአልሸባብ ጋር በሚያደርገው ውጊያም ድጋፍ ትሰጣለች። የምርጫ የጊዜ ሰሌዳውን በማያከብሩ ስማቸው ባልተገለጸ ማዕቀብ እና የቪዛ ዕገዳ ጥላለች።

XS
SM
MD
LG