አዲስ አበባ —
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጁቡቲ ያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ዓላማ ትብብር ዘርፎችን አጠናክሮ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በጅቡቲ በሚካሄድ የወደብ ልማት በጋራ እንድትሳተፍ ጅቡቲም በተመረጡ የኢትዮጵያ ተቋማት ድርሻ እንዲኖራት ከመግባባት ላይ መደረሱን አመልክቷል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ግንኑነት አስመልከቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መለስ ዓለምና ያነጋገረው እስክንድር ፍሬው ዘገባ ልኳል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ