በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት አብደልካደር ቴቡኒ ቃለ መሃላ ፈጸሙ


አብደልካደር ቴቡኒ አዲሱ የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ።

አልጄሪያ ባለፈው ሳምንት በተካሄደውና ተቃዋሚዎች ልሂቃኑ ሥልጣን የሙጥኝ ብለው ለመቆየት ያደረጉት ሙከራ ባሉት ምርጫ አሸንፈው ነው።

ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ታቡን ሃምሳ ስምንት ከመቶ ድምጽ አግኝተው ነው የተመረጡት። ዳሩ ግን የፖለቲካ ለውጦች እንዲካሄዱ በመጠየቅ ለአስር ወራት ሰልፍ ሲያካሂዱ የቆዩት ዜጎች በምርጫው አልተሳተፉም።

በተቃውሞ ሰልፉ ባላፈው ሚያዝያ የረጅም ጊዜው መሪ አብደላዚዝ ቡተፍሊካን ከሥልጣን እንዲወገዱ ረድቷል። ነገር ግን አዲስ መሪ ቢሚረጥም ሰልፉ አልተገታም።

ታቡኔ የሀገሪቱ ትልቁ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ቢሆኑም እንደሚዋጉ ከፓርቲው ወገንተኝነት ነጻ እንደሚሆኑ ቃል በመግባት ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ድጋፍ ለማግኘት ሲሞክሩ ቆይተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG