በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንጎ በኢቦኢላ ወረርሽኝ አንድ ሰው መሞቱ ተገለፀ


ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ውስጥ ዳግመኛ በተቀሰቀሰ የኢቦኢላ ወረርሽኝ፣ ሰሞኑን ደግሞ ሌላ አንድ ሰው መሞቱ ተገለፀ።

ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ውስጥ ዳግመኛ በተቀሰቀሰ የኢቦኢላ ወረርሽኝ፣ ሰሞኑን ደግሞ ሌላ አንድ ሰው መሞቱ ተገለፀ። ይህም፣ የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር እንዳረጋገጠው፣ በወረርሽኙ የሞቱትን ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር አሥራ ሁለት ያደርሰዋል።

የአሁኑ ህመምተኛ የሞተው፣ በሰሜናዊ ምዕራብ የኢኳተር ክፍለ ሀገር ውስጥ በምትገኘው ገጠሪቱ የኢቦኮ መንደር ውስጥ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚንስቴሩ አመልክቶ፣ ሌሎች አራት ሰዎች ህመሙ እንዳለባቸው የሚጠረጠሩ መሆናቸውንም አክሎ ገልጧል።

በአሁኑ ወቅት፣ በኮንጎ 32 የተረጋገጡ የኢቦላ ህሙማን እንዳሉም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG