በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የኮንጎ ፕሬዚዳንት ቃለ መሃላ ፈፀሙ

አዲስ የተመረጡት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሰኬዲ ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር በሚያሰሙበት ሰዓት ላይ ግን በህመም ምክንያት ንግግራቸውን አቋርጠው እንደነበር ተዘግቧል።

አዲስ የተመረጡት የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሰኬዲ ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር በሚያሰሙበት ሰዓት ላይ ግን በህመም ምክንያት ንግግራቸውን አቋርጠው እንደነበር ተዘግቧል።

በሺዎች የተቆጠሩ የአዲሱ ፕሬዚዳንት ደጋፊዎችና ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ኪንሻሳ ከተማ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

ሺሰኬዲ መናገር ጀምረው ነበር የብሄራዊው ቴሌቪዥን ካሜራዎች ግን ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን ከማብቃታቸው በፊት ትኩረታቸውን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዙረዋል።

የፕሬዚዳንቱ ረዳቶች በዚህ መሃል ደጋግፈው እንዲቀመጡ ማድረጋቸውንና ውሃ እንዳቀበሏቸው ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ዘገባው አክሎም - ሺሰኬዲ ላፍታ ካረፉ በኋላ ወደ ፖዲየሙ ተመልሰው ንግግራቸውን ያቋረጡት በተራዘመው የምርጫ ሂደት በመዳከማቸውና የወቅቱ ሁኔታ በፈጠረባቸው የደስታ ስሜት ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

የ55 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሺሰኬዲ - የረዥም ጊዜ የኮንጎ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ልጅ ሲሆኑ የዩዲፒኤስ ፓርቲ መሪ ናቸው።

በኮንጎ የ60 ዓመታት ታሪክ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ ሲሸጋገር ይህ የዛሬው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG