በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጤና ማዕከሉ ተጨማሪ ክትባት ከከፋ ህመምና ሆስፒታል ያድናል አለ


ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ-19 ክትባት እና ማጠናከሪያ መስጫ የጎዳና ላይ አገልግሎት ኒው ዮርክ እአአ ዲሴምበር 2/2022
ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ-19 ክትባት እና ማጠናከሪያ መስጫ የጎዳና ላይ አገልግሎት ኒው ዮርክ እአአ ዲሴምበር 2/2022

በዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕክል ትናንት ማክሰኞ የወጣ አንድ ጥናት፣ የኮቪድ-19 ተጨማሪ ክትባት፣ ከከፋ ህመምና ሆስፒታል ከመግባት የሚያድን ተጨባጭ ውጤት የሚያሳይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የፌዴራሉ የጤና ተቋም ከዚህ ድምዳሜ የደረሰው ሎስ አንጀለስ ውስጥ ካለፈው ህዳር እስከ ጥር ወር ድረስ ለዴልታ እና ኦሚክሮን ቫይረስ በተጋለጡ ከ400ሺ አዋቂ ሰዎች ላይ ባደረገው ምርምር መሆኑን አስታውቋል፡፡

በተባለው ጊዜ ውስጥ ክትባቱን ያልወሰዱና ለዴልታ ቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ክትባቱን ከወሰዱት ይልቅ 83 ጊዜ እጥፍ መታመማቸውና ሆስፒታል መግባታቸው በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

በጥር ወር ውስጥም በኦሚክሮን ቫይረስ በተጋለጡ ሰዎች ላይ በተወሰደ ጥናት የማጠናከሪያውን ከትባት ከወሰዱት ይልቅ ያልተከቡት 23 ጊዜ እጥፍ ወደሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG