በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ አራተኛው ዙር ወረርሽኝ እየቀነሰ ሲመጣ የተጋላጮችም ቁጥር ቀንሷል


የጤና ባለሞያዋ የኮቪድ ክትባት ስትሰጥ፣ ናይሮቢ፤ ኬንያ ጃንዋሪ 20/2022
የጤና ባለሞያዋ የኮቪድ ክትባት ስትሰጥ፣ ናይሮቢ፤ ኬንያ ጃንዋሪ 20/2022

በአፍሪካ ከኦሚክሮን ቫይረስ ጋር በተያያዘ አራተኛው የኮቪድ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የሚደርሰው ሳምንታዊ የሟቾች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

በያዝነው የጥር ወር ሳምንት ውስጥ በወረርሽኙ የተጋለጡ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በ20 ከመቶ መቀነሱንም ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን መሆን ከሚገባው አንጻር ገና በመሆኑን ከፍተና ክትልል የሚያሻው ጉዳይ መሆኑንም የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በአፍሪካ በኦሚክሮን ወረርሽኝ ተጠቂዎችና ሟቾች ቀዳሚ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ ባለፉት አራት ሳምንታት የሟቾችም ሆነ የተጋላጮች ቁጥር ማሽቆልቆሉን አመልክቷል፡፡

በአፍሪካ ውስጥ ቁጥሩ ጨምሮ የታየው በሰሜን አፍሪካ መሆኑን ገልጾ 55 ከመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቋል፡፡

በተቀረው የአፍሪካ ክፍል የአዳዲስ ተጋላጮች ቁጥር እኤአ እስከ ጥር 16 ድረስ 10.4 ሚሊዮን መሆኑና የሟቾች ቁጥር 233ሺ መሆኑን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG