አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የካቢኔ ሹም ሽር አካሂደዋል፡፡ ከ28ቱ ሚኒስትሮች አብዛኞቹ፣ ማለትም አሥራ ስምንቱ በአሉበት ቀጥለዋል ወይንም በሌላ መሥርያ ቤት በተመሳሳይ ኃላፊነት ተሹመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮቹን ሹመት ያፀደቁት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ኅብረተሠቡን ማማረርና የሙስና ተግባር ሊታለፉ የማይገባቸው ቀይ መሥመሮች መሆናቸውንም በማሳሰብ ጭምር ነው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ