በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን ዐዋጅን ያሻሽላል የተባለ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ


የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን ዐዋጅን ያሻሽላል የተባለ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00

የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን ዐዋጅን ያሻሽላል የተባለ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ

በፌደራል የመንግሥት መሥሪያ ቤት፥ “ኢትዮጵያን የሚመስል የሠራተኞች ሥብጥር መኖሩን የሚያረጋግጥ”፣ “የብሔር ብሔረሰቦችን ብዙኀነት እና አካታችነት” ያገናዘበ ሥርዓት ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት የሚደነግግ የዐዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ።

የዐዋጁ ረቂቅ፣ ላለፉት ስድስት ዓመታት በሥራ ላይ ያለውን የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች ዐዋጅ ቁጥር 1064/2010ን የሚያሻሽል ነው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያናገራቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ አስተዳደር እና ልማት አመራር ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር አደም ከድር፣ ዐዋጁ በቂ ውይይትን እንደሚፈልግ ገልጸው፣ በትክክል ተግባራዊ ለማድረግም አስቀድሞ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ማካሔድ አስፈላጊ ስለመኾኑም ይናገራሉ፡፡

ዐዋጁ፣ አንድን ቡድን ብቻ ለመጥቀም እንዳይውል ማድረግና ምደባው፥ የሥራ ችሎታንም ማዕከል ባደረገ መልኩ እንዲከናወን የሚያስችሉ ኹኔታዎች መኖራቸውንም ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG