በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳያርሱ መዝራት፡- አዲስ የእርሻ ዘዴ ለኢትዮዽያውያን ገበሬዎች


በኢትዮጵያ “ሳያርሱ መዝራት” የተባለው አዲስ የእርሻ ዘዴ ገበሬዎች እንዲለምዱት የምርምርና የሙከራ ስራ በመካሄድ ላይ ነው።

ይህንኑን ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ እየተመራመሩ ያሉት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በቤልጅየም በሚገኘየው ጌንት ዩኒቨርሲቲ የፒ. ኤቺ. ዲ. መርሃ ግብር እየሰሩ ያሉት አቶ ተስፋይ ኣርኣያ ናቸው።

አቶ ተስፋይ ሳያርሱ መዝራት በሶስት መንገዶች ይከናወናል ብለዋል። አንድን ማሳ በአመት አንድ ጎዜ ብቻ ማረስ፣ እህል ሲታጨድ 30 ከመቶ የሚሆነውን ተረፈ ምርቱን እዛው ማሳ ላይ ማስቀረት፣ እንዲሁም በአንድ ማሳ ላይ የተለያዩ እህሎችን እያፈራረቁ መዝራት እንደሆነ ገልፀዋል።

ሳያርሱ የመዝራት ዘዴ በአሜሪካ እንደተጀመረና በላቲን ኣሜርካ እንደ ብራዚል እና አርጀንቲና ባሉት ኣገሮች በስፋት እንደሚታወቅ ተመራማሪው ይናገራሉ። በአሁኑ ዘመን በአለማችን ከ100 ሚልዮን በላይ ሄክታር መሬት በዚሁ ዘዴ ይታረሳል።

ሳያርሱ በመዝራት መሬትን በጎርፍ በቀላሉ ከመሸርሸር ማዳን ይቻላል። በያመቱ ተረፈ ምርቱን መሬት በመተው የመሬትን ለምነት ማስጠበቅ እና ጥሩ ምርት ይገኝበታል ብለዋል ኣቶ ተስፋይ።

ምርምሩን በሚያካሂዱበት በትግራይ ክልል የደጉዓ ተምቤን እና የዓዲ ጉዶም ወረዳዎች ገበሬዎች ለብዙ ሺዎች አመታት በሚጠቀሙበት ያስተራረስ ዘዴ ከኣንድ ሄክታር መሬት በመሸርሸ 250 ኩንታል አፈር ይባክን የነበረው የአፈር መጠን ወደ 50 ኩንታል ዝቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG