በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለውጥ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋም


የአሜሪካ ድምጽን ጨምሮ አምስት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የመገናኛ አውታሮችን የሚያስተዳድረው የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ሚዲያ (ዩ ኤስ ኤ ጂ ኤም) አዲሷ ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ የተሰናባቹን ፖሊሲዎች ፈጥነው እየቀለበሱ ናቸው።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ሳምንት ቃለ መሃላቸውን ከፈጸሙ በኋላ በዚያው ዕለት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሚድያ ተቁዋሙን እንዲመሩ የተሾሙትን ማይክል ፓክን ከስራው እንደሚያባርሩዋቸው ካስታወቁዋቸው በኋላ ፓክ ስራቸውን ለቀዋል።

በርሳቸውም ምትክ በተቋሙ ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚነት በዋይት ሃውስ የተሾሙት ኬሉ ቻዎ በአሜሪካ ድምጽ በጋዜጠኝነት እና በበላይ ኃላፊነት ደረጃ በጠቅላላው ከአርባ ዓመታት በላይ ተመክሮ ያላቸው ሲሆኑ የዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋሙን ለመምራት የበቁ የመጀመሪያ ሴት ናቸው።

አዲሷ ሥራ አስፈጻሚ በተሰናባቹ የአሜሪካ ድምጽ ዳይሬክተርነት ተሹመው የነበሩትን ሹመታቸው ብርቱ ነቀፌታ አስከትሎ የከረመውን ሮበርት ራይሊን አሰናብተዋቸዋል።

የቪኦኤዋ ጄሲካ ጃረትን ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ለውጥ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋም
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:57 0:00


XS
SM
MD
LG