ዋሺንግተን ዲሲ —
በኮቪድ-19 ስጋት ምክንያት የኒው ዮርክ ከተማ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ዛሬ አዘጋጆቹ ይፋ አደረጉ።
የኒው ዮርክ ማራቶን በመጪው ኅዳር ወር 50ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ዝግጅት ላይ ሃምሳ ሺህ ሯጮች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካቾችና 10ሺህ በጎ ፈቃደኞች ያሰባሰባል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በአሳሳቢ ደረጃ እየተዛመተ መሆኑንና ከበጋው በኋላ በሚመጡት ወራት ደግሞ 2ኛ ዙር ወረርሽኝ ይከተላል የሚል ሥጋት በመኖሩ ለህዝብ ጤና ሲባል የኒው ዮርክ ከተማ ባለሥልጣናት እና ዝግጅቶቹን የሚያደራጀው ኒው ዮርክ ሮድ ራነርስ የተባለው ድርጅት ከውሳኔው መድረሳቸው ተገልጿል።