በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኒው ዮርክ ጤናው ዘርፍ ሠራተኞች መከተብ ግዴታ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የጤና ባለሞያዎች በኒው ዮርክ
ፎቶ ፋይል፦ የጤና ባለሞያዎች በኒው ዮርክ

በኒው ዮርክ ለሚገኙ ሆስፒታሎችና በአረጋውያን መንከባከቢያ ተቋማት ወይም ነርሲንግ ሆም ውስጥ ለሚሰሩት የጤና ሠራተኞች በሙሉ እንዲከተቡ በግዛቲቱ መንግሥት የተቀመጠው ቀነ ገደብ በዛሬው እለት ያበቃል፡፡

ከዚህ ውጭ ቤት ውስጥ የሚሰጠውን የጤና እንክብካቤ የሚሰጡና በሌሎች ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት የሚሰሩ ሌሎች ሠራተኞች ደግሞ እስከ መስከረም 27 ድረስ መከተብ ይኖርባቸዋል፡፡

የኒው ዮርክ ገዢ ካቲ ሆቹል የተቀመጠውን መመሪያና የክትባት ቀነ ገደብ ባለማክበር የማይከተቡ የጤናው ዘርፍ ሠራተኞችን መቆጣጠር የሚያስችል ችግር ቢኖር በህክምናው ሥልጠና ያላቸው የብሄራዊ ክብር ዘብ አባላትን እንደሚያሰማሩ አስታውቀዋል፡፡

በቂ የሀኪም ማረጋጋጫ ሳይኖራቸው ክትባቱን መውሰድ ያልፈልጉ ሰዎች ከሥራቸው የሚታገዱና የሥራ መፈለጊያ ጥቅማ ጥቅሞችንም እንዳማያገኙ የክልሉ ገዥ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

እስከ መስከረም 22 ድረስ በኒዮርክ ከሚገኙ ሆስፒታሎች በሙሉ የተከተቡት ሠራተኞች 84 ከመቶ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG