በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኔዘርላንዱ “ዶናልድ ትረምፕ” በምርጫ ከፍተኛ ድል ተቀዳጁ


የኔዘርላንዱ ፖለቲከኛ ጊርት ዋይልደርስ
የኔዘርላንዱ ፖለቲከኛ ጊርት ዋይልደርስ

የእስልምና እምነት ተከታዮችን በማጥላላት የሚታወቁት እና ፍልሰተኞች ወደ አገራቸው እንዳይገቡ በምርጫ ዘመቻቸው የተሟገቱት የኔዘርላንዱ ፖለቲከኛ ጊርት ዋይልደርስ፣ በትናንቱ የኔዝርላንድ ምርጫ ከፍተኛ ድል በመቀዳጀታቸው፣ የገዢ ፓርቲው የጥምር መንግስት እንዲመሠረት ሊያስገድዱ እና ምናልባትም ቀጣዩ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ እንደሚችሉም በመነገር ላይ ነው።

በእስልምና አክራሪዎች በርካታ የግድያ ዛቻ የደረሰባቸው፣ ሞሮኳውያንን በመስደባቸው በፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉት እና በአንድ ወቅትም እንግሊዝ ወደ አገሯ እንዳይገቡ ያገደቻቸው ፖለቲከኛ፤ በሕዝባዊ ፖሊሲያቸው እና ከአነጋገርቸው ቁጥብ ባለመሆናቸው፣ እንዲሁም የጸጉራቸው መመሳሰል “የኔዘርላንዱ ትረምፕ” የሚለውን ስም አሰጥቷቸዋል።

ጊርት ዋይልደርስ ሌሎች ፖለቲከኞችን ከማጥላላታቸው እና እንዲገለሉ ከማድረጋቸው በተጨማሪ፣ በጸረ-እስልምና ንግግራቸው ምክንያት ከእስልምና አክራሪዎች ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል። በዚህም ምክንያት ለዓመታት የ24 ሰዓታት ጥበቃ እንዲያስፈልጋቸው አስገድዷል።

በእ.አ.አ 2009 ዓ/ም ጊርት ዋይልደርስ፤ ቁራንን “ፋሺስት መጽሓፍ” ብለው የጠሩበትን እና ያዘጋጁትን ፊልም፣ አንድ የእንግሊዝ የላይኛው የመኳንንቶች ፓርላማ አባል ቀርበው እንዲያሳዩ መጋበዛቸውን ተከትሎ፣ መንግስት “በማሕበረሰቡ አብሮ የመኖር እና ደህንነት” ላይ ስጋት የደቀኑ ግለሰብ ናቸው በሚል ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ አግዷቸው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG