በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በነቀምቴ የመንግሥት የሥራ ኃላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ


በኦሮምያ ጤና ቢሮ የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
በኦሮምያ ጤና ቢሮ የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

የነቀምቴ ከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከትናንት በስቲያ መገደላቸውን እና የገዳዮቹ ማንነት አለመታወቁን የከተማው ጸጥታና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ ከግድያው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አሥር ሰዎች መታሰራቸውን ተናግረዋል።

የከተማው የሥራ ዕድል ፈጠራ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፈይሳ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በመንግሥት ሥራ ላይ ቆይተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከጀርባቸው በተተኮሰው ጥይት መገደላቸውን የከተማው ጸጥታና አስተዳደር ጽሕፈት ኃላፊ አቶ ምስጋኑ ዋቅጋሪ ተናግረዋል።

አቶ ምስጋናው አያይዘው፤ “ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች አቶ መልካሙ ላይ ጥይት ካዘነቡ በኋላ 03 ቀበሌ ውስጥ ወልዳ አራራ ቤተክርስቲያን አካባቢ ደርሰን በፍጥነት ወደ ነቀምቴ ሆስፒታል ብንወስደውም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።” ብለዋል።

ከግድያው ጋር ተያይዞ አሥር ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና የገዳዮቹ ማንነት በምርመራ ላይ መሆኑን የገለፁት አቶ ምስጋናው፤ “ነቀምቴ ውስጥ መንግሥትን የሚቃወም ኃይል ታጥቆና ሲቪል መስሎ አልፎ አልፎ በመንግሥት አመራሮች ላይ ግድያ ሲፈጽም ቆይቷል። አቶ መልካሙንም የገደለው ይህ ኅይል ነው ብለን እንጠረጥራለን። ነገር ግን የሚረጋገጠው በፖሊስ ምርመራ ነው።” ብለዋል።

ባለፉት አራት ዓመታት በነቀምቴ ከተማ ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ አካላት ብዙ የመንግሥት ሥራ አመራሮችና ንጹሀን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን የምርመራ ሂደቱ ሥርሥር ጉዳይ በፖሊስ እጅ እንደሚገኘ አቶ ምስጋኑ ጨምረው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በነቀምቴ የመንግሥት የሥራ ኃላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:58 0:00


XS
SM
MD
LG