በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በነቀምቴ የንግድና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ


በነቀምቴ ከተማ ባለፈው አንድ ዓመት ገደማ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት የንግድና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና በማሳደሩ አንዳንድ ባለሃብቶች ወደ ሌላ ቦታ እየሄዱ እንደሚገኙ ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ገለፁ።

የኢንተርኔት አገልግሎትም በከተማው መቋረጡና በአብዛኛው የወለጋ ዞኖች የስልክ አገልግሎት አለመኖርም ሥራቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን እንዳንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ተናግረዋል።

የነቀምቴ ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስጌን ከተማዋ በአሁኑ ሰዓት ተረጋግታለች፣ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዋም እንዲቀላጠፍ ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን በምዕራብ ኦሮምያ ለሁለት ወራት የተዘጋውን የኢንተርኔትና ስልክ አገልግሎት መንግሥት እንዲከፍት ቢጠይቅም ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ዙርያ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በነቀምቴ የንግድና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:17 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG