በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌልትማን በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ዛሬ ወደ አረብ ኤምሬት ቱርክና ግብጽ እየሄዱ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ኔድ ፕራይስ
ፎቶ ፋይል፦ ኔድ ፕራይስ

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀን ልዩ ልኡክ አምባሳደር ፌልትማን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከኢትዮጵያ ምን እንደሚጠብቅ ለመምከር ዛሬ ሀሙስ ጀምሮ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬት፣ ቱርክ እና ግብጽ እንደሚያመሩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በትናንቱ መግለጫቸው አመልከተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ኔድ ፕራይስ የግጭቱ ዋነኛ መፍትሄ ድርድር መሆኑን አውስተው ወታደራዊ መፍትሄ የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ግጭቱ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ላይ አደጋ መደቀኑንም ገልጸዋል፡፡

"አምባሳደር ፌልትማን የሚመሩትም ሆነ የኛ ተዕልኮው ዋነኛ ግብ፣ ዲፕሎማሲን የመጀመሪያ፣ የመጨረሻና ብቸኛ አማራጭ በማድረግ ግጭቱንና እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስቆም" መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG