በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ ተቃውሞ በኢትዮጵያ


ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ
ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ

ያለፉ ሃያ ዓመታት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተቃውሞ ታሪክ ከ1997ቱ የስኬት እንቅስቃሴ ሌላ የመሣደድና የድክመት እንደነበር የቀድሞ የተቃውሞ መሪ ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ አስታውቀዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትምህርት ላይ የሚገኙት ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ ባለፈው ሣምንት ዋሽንግተን ውስጥ የዴሞክራሲ ውርስ /ኢንዳውመንት ፎር ዴሞክራሲ/ የተባለ ተቋም ባዘጋጀው መድረክ ላይ ቀርበው ላይ ተናግረው ነበር፡፡

ወ/ት ብርትኳን በሦስት ምዕራፍ ከፍለው ባቀረቡት ፅሁፍ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ዳራ፣ ከኢሕአዴግ ወደ ሥልጣኑ መድረክ መውጣት ጋር የብዝኀ ፓርቲ ሥርዓት ዕውቅና ማግኘት፣ ወዲያውም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወከባና መሣደድ ስለመጀመሩና እራሣቸውን የማጠናከሪያና የማደራጃ እፎይታና የተሣትፎ መድረክ አለማግኘታቸውን አስረድተዋል፡፡

ኢሕአዴግ “ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ” ባሉት ግን ባልተናገሩት ምክንያት የ1997ቱን ምርጫ ፍትሐዊና ነፃ ለማድረግ መወሰኑንና ተቃዋሚዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው ሕዝቡን ማነቃነቃቸውንና መሠረት ማግኘታቸውን፣ ችግር በበዛበት ሁኔታ እንኳ 172 ዕውቅና የተሰጠው መቀመጫ መቀዳጀታቸውን፣ ከዚያ ትምህርት የወሰደው ኢሕአዴግ ከ1997 ምርጫ በኋላ አምባገነንነቱ ይበልጥ መክፋቱን ተናግረዋል፡፡

ለቀሪው ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG