በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብርትኳን ሚደቅሣ በዴሞክራሲ ውርስ ተቋም


ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ
ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ፤ መነሻና አቅጣጫ ላይ ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃውሞን ለማፈን ተግባር ይውላል ያሉት በቢሊዮኖች የሚቆጠር የዋና ዋና ለጋሾች ገንዘብ ይበልጥ ውጤታማ ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ አሜሪካ ውስጥ በትምህርት ላይ የሚገኙት የቀድሞ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ መሪ ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የዴሞክራሲ ባሕል በተቀዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ይሠርፅ ዘንድ የፖለቲካ ፕሮግራሞቻቸውን እንደገና ፈትሸው ማደራጀት ይገባቸዋል ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል፡፡

ወ/ት ብርትኳን ይህንን አስተያየት የሰጡት “ብሔራዊ የዴሞክራሲ ውርስ” (ENDOWMENT FOR DEMOCRACY) የተባለው ዋና መሥሪያ ቤቱ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሆነ ተቋም ትናንት ባዘጋጀው የውይይት ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው፡፡

መድረኩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን መገንባት በሚል ርዕስ ነበር፡፡ በዚህ መድረክ ላይ ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣ ለ32 ደቂቃ ያክል የዘለቀው ማብሪራያቸው በጥናት መረጃዎች የተደገፈ ነበር፡፡

በሦስት ክፍሎች አደራጅተው ባቀረቡት ፅሁፋቸው ወ/ት ብርትኳን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ አንሰተው በ1997ቱ ምርጭ ወቅት ፓርቲዎች የተጫወቱትን ሚና አብራርተዋል፡፡

በዚህ ክፍል ውስጥ ከ1997 ምርጫ በኋላ የተከሰቱና “የአምባገነንነቱ ይበልጥ መክፋት” ያሉበትን ገፅታ አሳይተዋል፡፡

በሁለተኛው የማብራሪያቸው ክፍል ከመጀመሪያው ክፍል በመነሣት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጋፍጠዋቸዋል፤ ወይም አሉባቸው ያሏቸውን ችግሮችና አንዳንድ መሠረታዊ ምንጮቻቸው ያሏቸውን ሃሣቦቻቸውን ሠንዝረዋል፡፡

በሦስተኛው የማብራሪያቸው ክፍል ውስጥ “የተግባር ሃሣቦች” ያሏቸውን የመፍትሔ መንደርደሪያዎች አቅርበዋል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም በዳያስፖራ ያለው ኢትዮጵያዊ፣ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብና የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እራሣቸውም ሊያከናውኗቸው ይገባል የሚሉትን ጠቋሚ ሃሣብ ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG