በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ ቦርድ ውጤቱን በሁለት ቀናት ያሳውቃል


የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ
የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ

ሁሉም የምርጫ ክልሎች በሁለት ቀናት ውስጥ የምርጫውን አሸናፊዎች እንደሚያሳውቁ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። በምርጫው ቀን የነበሩ ተግዳሮቶችን በተመለከተ ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ አይነት በርካታ አቤቱታዎችን መቀበሉን የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልጸዋል፡፡

ቦርዱ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ በሚገኘው ነጌሌ የምርጫ ክልል ድምጽ እንዳይሰጥ አግዶ የነበረ ቢሆንም በዕለቱ ድምጽ መሰጠቱንም የተናገሩት ወ/ሪት ብርቱካን፣ ጉዳዩ መሕግ እንደሚታይ ገልጸው በስፍራው የተካሔደው ምርጫ ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ምርጫ ቦርድ ውጤቱን በሁለት ቀናት ያሳውቃል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00


XS
SM
MD
LG