በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍርድ ቤት በህወሓት ስም ዐዲስ ፓርቲ ለማቋቋም የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገው


የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት
የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ‘ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ’/‘ህወሓት’/ በሚል መጠሪያ፣ ዐዲስ ፓርቲ መመሥረት እንደማይቻል ያሳለፈውን ውሳኔ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤትም አጸናው፡፡

‘ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ’/‘ህወሓት’/ በሚል ስም፣ ዐዲስ ክልላዊ ፓርቲ የማቋቋም የቅድመ ዕውቅና ፈቃድ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸውና ውሳኔውን ተቃውመው የይግባኝ አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት በእነገብረ ሚካኤል ተስፋዬ እና በብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ መካከል ሲደረግ የነበረ ክርክር መቋጨቱን፣ ቦርዱ ዛሬ፣ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እነገብረ ሚካኤል ተስፋዬ፣ ‘ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ’(‘ህ.ወ.ሓ.ት’) ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት፣ በ120 መሥራች አባላት ፊርማ የተደገፈ የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ፣ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም.፣ለምርጫ ቦርድ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በተጠቀሰው ስያሜ የሚጠራ፣ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ እንደነበረ ያስታወሰው፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት፣ በዚኹ ስም ዐዲስ ፓርቲ ማቋቋም፣ መራጩን የሚያደናግር በመኾኑ፣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም.፣የቅድመ ዕውቅና ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ፣ “ስሕተት አይደለም፤” ሲል ውሳኔውን አጽንቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG