በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን 230ሺሕ ሕፃናት በረሃብ ሊሞቱ ይችላሉ ተባለ


ፎቶ ፋይል፦ በሱዳን ጦርነቱን ሸሽተው ምሥራቃዊ አድሬ ከተማ ቻድ አቅራቢያ በሚገኘው ኦውራንግ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የዓለም አቀፍ የዕርዳታ ዕርዳታን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ሱዳናውያን
ፎቶ ፋይል፦ በሱዳን ጦርነቱን ሸሽተው ምሥራቃዊ አድሬ ከተማ ቻድ አቅራቢያ በሚገኘው ኦውራንግ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የዓለም አቀፍ የዕርዳታ ዕርዳታን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ሱዳናውያን

አስቸኳይ ርዳታ ካልተደረገ፣ በጦርነት በደቀቀችው ሱዳን 230 ሺሕ የሚሆኑ ሕፃናትና አራሶች በረሃብ ሊሞቱ ይችላሉ ሲል የተመድ የሕፃናት አድን ድርጅት አስታውቋል።

አስራ አንድ ወራት ባስቆጠረውና በሁለት ተቀናቃኝ ጀኔራሎች መካከል በሚካሄደው ጦርነት ሳቢያ፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ተፈናቅለዋል።

የቦምብ ድብደባው ፣ የእርሻ ማሳዎችና ፋብሪካዎች ውድመት ሱዳንን በዓለም ላይ ካሉ አስከፊ የምግብ ቀውስ ውስጥ ከሚገኙ ሀገራት እንድትመድ እንዳደረጋት በሱዳን የሕፃናት አድን ድርጅቱ ዲሬክተር አሪፍ ኑር ተናግረዋል።

“230ሺሕ የሚሆኑ ሕፃናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች እና አራሶች በመጪዎቹ ወራት ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ” ሲል የእንግሊዙ የሕፃናት አድን ድርጀት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።

በሱዳን ከ2.9 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ለአስከፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጋለጣቸውን እና 729ሺሕ የሚሆኑና ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ደግሞ ለአደገኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መዳረጋቸውን በጎ አድራጊ ድርጀቱ ጨምሮ አስታውቋል።

በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት በዓለም ትልቁን የረሃብ ቀውስ ሊቀሰቅስ ይችላል ሲል የዓለም የምግብ ፕሮግራም በቅርቡ አስጠንቅቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG