በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቃለ ምልልስ ከነአምን ዘለቀ ጋር


የዛሬው የዲሞክራሲ በተግባር እንግዳ በቅርቡ የተመሠረተው ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ አባልና ከአስተባባሪዎቹ አንዱ አቶ ነዓምን ዘለቀ ናቸው።

ንቅናቄው በአራቱ ዋና ዋና የሀገሪቱ ቋንቋዎች በአማርኛ፥ በኦሮምኛ፥ በትግርኛና በሱማልኛ - በቃ፥ ገኤ፥ ይአከል፥ ባስ የሚል መፈክር አንግቧል።

"በቃ ስንል - ይላሉ አቶ ነዓምን - ዘረኝነት በቃ፥ አምባገነንነት በቃ፥ ድህነት በቃ፥ ማን አለብኝነት ይብቃ፥ ፍትሕ-አልባው ሥርዓት ይብቃው፥ የሃያ ዓመታቱ የወያኔ አገዛዝ ያብቃ ማለታችን ነው።"

«መልዕክቱን ለማድረስ በዋናነት የምንፈልገው፥ ለኢትዮጵያ ሕዝባችን ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በራስ ተነሳሽነት በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ እራሡን እያደራጀ ይገኛል። ለነፃነትና ፍትሕ ጥማት እንዳለው ለመረዳት ችለናል። ከያካባቢው የምናገኛቸው መረጃዎችም፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልክ እንደ ቱኒዝያና ግብፅ ሕዝቦች ይህንን አስከፊ ሥርዓት ለመጣል ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊንቀሳቀስ እንደሚችል የሚጠቁሙ ናቸው። በዚሁ መሠረት ከሕዝባችን ጐን ለመቆም እንፈልጋለን» ሲሉም አቶ ነዓምን ዘለቀ ያስረዳሉ።

ዝርዝሩን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG