ዋሺንግተን ዲሲ —
"ህወሃት ጀምሮታል" ያለውን ማጥቃት እየመከተ መሆኑን ትናንት ባወጣው መግለጫ የጠቀሰው የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር "ወረራውን በማያዳግም ሁኔታ እንቀለብሳለን” ብሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ "ተዋጊዎቻቸው ድል እየቀናቸው" መሆኑን መንግሥቱ በሽብርተኝነት የፈረጀው የህወሃት ቃል አቀባይ ዛሬ በትዊተር ገፃቸው በጻፉት መልዕክት አስፍረዋል፡፡
ወገኖቹ ተኩስ እንዲያቆሙና ወደ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲዞሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት መጎትጎታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወታደራዊ መፍትሄ እንደማይታያቸው ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡