በውይይቱ ከተሳተፉ አስተያየት ከሰጡት መካከል ናቸው፡፡ በብሔራዊ መግባባት ላይ ትኩረት በማድረግ በተወካዮች ምክር ቤት በተካሔደ ውይይት ላይ፣ ለሂደቱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ግጭቶች መቆም እንዳለባቸው ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡
ከተሳታፊዎች መካከል አስተያየት የሰጡት አንድ የኢትዮጵያ መከላከያ ጄኔራል “ከዚህ በኋላ እኛም ህዝቡም እንዲበጠበጥና እንድንሰዋ አንፈልግም ቁጭ ብላችሁ ችግራችሁን ፍቱ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሥራ ጊዜው በመገባደድ ላይ የሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አር አያ፣ አስቻይ ሁኔታዎች ባለመኖራቸው ሂደቱ እየፈተነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተነሱት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ላይ፣ ለውይይቱ የመነሻ ጥናታዊ ጹሑፎችን ያቀረቡ አካላትና የመንግሥት ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መድረክ / ፎረም