በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተጨማሪ ሚስጥራዊ ሰነዶች በባይደን መኖሪያ ቤት ተገኙ


ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ

ዴላዌር በሚገኘው የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መኖሪያ ቤት ተጨማሪ ሚስጥራዊ ሰነዶች መገኘታቸውን የፕሬዚዳንቱ ጠበቃ ትናንት አስታወቁ።

በሳምንቱ መጀመሪያ ጆ ባይደን ቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት 'ጥብቅ የሀገር ሚስጥር' ተብለው የተለዩ ሰነዶች፣ ከሥልጣናቸው ከወረዱ በኃላ ዋሽንግተን ውስጥ እንደ ቢሮ ይጠቀሙበት በነበረ አንድ የጥናት አጥኚዎች ስብስብ ተቋም ውስጥ የመገኘቱ ዜና ይፋ ከተደረገ በኃላ ለዋይት ኃውስ አሳፋሪ ሳምንት ሆኖ ቆይቷል።

ጉዳዩን አስመልክቶ ሐሙስ ዕለት የተናገሩት ፕሬዚዳንት ባይደን ጠበቆቻቸው ሚስጥራዊ ሰነዶቹን ፈልገው እንዳገኙ እና እንዳስረከቡ ተናግረዋል።

ባይደን "ሚስጥራዊ ሰነዶችን በቁም ነገር እንደማያቸው ሰዎች ያውቃሉ ከፍትህ መስሪያ ቤቱ ጋርም ሙሉ ለሙሉ እየተባበርን ነው" ብለዋል።

ሆኖም የሪፐብሊካን መሪዎች - ኤፍቢአይ - የተሰኘው የፌዴራል የምርመራ ቢሮ ፍሎሪዳ በሚገኘው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻ ባካሄደበት ወቅት ዲሞክራቶች ትራምፕ ላይ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።

የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ የፍትህ ሚኒስቴር በባይደን እጅ የተገኙትን 'ጥብቅ የሀገር ሚስጥር' ማህተም የተደረገባቸውን ሰነዶች የሚመረምር ልዩ አማካሪ እንደሚሾም ትናንት አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች የሥልጣናቸው ዘመን ሲያበቃ የተጠቀሙባቸው ሚስጥራዊ ሰነዶች ወደ ብሄራዊ ቤተ መዛግብት እንጂ ወደሌላ ቦታ መሄድ እንደሌለባቸው የዩናይትድ ስቴትስ ህግ ያዛል።

XS
SM
MD
LG