በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው ተቃዋሚ ናቫልኒ የ9 ዓመት እስር ተፈረደባቸው


ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰው አሌክሲ ናቫልኒ
ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰው አሌክሲ ናቫልኒ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰው የሆኑትና ቀደም ሲል ከተመረዙበት አደጋ በማገገም ወደ ሩሲያ የተመለሱት አሌክሲ ናቫልኒ በተከሰሱበት የማጭበርበርና የመዳፈር ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውን በመበየን የ9 ዓመት እስር የፈረደባቸው መሆኑን አስታወቀ፡፡

በናቫልኒ ላይ የተላለፈው እስር ቀደም ሲል በተመሰረተባቸው ክስ ታስረው የቆዩበትን የ2ዓመቱ ተኩል ጋር አብሮ የሚቆጥርላቸው ስለመሆኑ አልተገለጸም፡፡

የ45 ዓመቱ ናቫልኒ ከእስራቱ በተጨማሪ የ11ሺ500 ዶላር የገንዘብ ቅጣት የተፈረደባቸው መሆኑንም ተገልጿል፡፡ ናቫልኒ ከተመሰረተባችው ክስ መካከል ለፖለቲካ ሥራ ደጋፊዎቻቸው የሰበሰቡትን ወደ 33ሺ ዶላር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የሚል ይገኝበታል፡፡

የሩሲያ ባለሥልጣና ናቫልኒ ከምዕራባውያን ጋር በመተባበር በሩሲያ አለመረጋጋት እንዳይኖር ይሰራሉ ሲሉ ይከሷቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG