ዋሺንግተን ዲሲ —
የሩስያው ተቃዋሚ መሪ አሌክስ ናቫኢኒ፣ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሕዝቡ እንዳይሳተፍ ጥሪ ማድረጋቸው ህገ ወጥ ሊሆን ይችላል" ሲሉ፣ አንድ የክሬምሊን ቤቴ መንግሥት ቃል አቀባይ ተናገሩ።
ናቫልኒ፣ እአኤ በመጪው መጋቢት 18 ቀን በሚካሄደው ምርጫ ሕዝቡ ድምፅ እንዳይሰጥ ጥሪ ያስተላለፉት፣ የምርጫ ኮሚሽን ባለሥልጣናት፣ በትናንቱ ዕለት ከውድድሩ ስላገዷቸው መሆኑም ታውቋል።
የሩስያው ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚሽን፣ ፀረ ሙስና የድረ ገጽ ዘመቻ የሚያካሂዱት ናቫልኒ "በወንጀል የተከሰሱ ናቸው" በሚል፣ ከውድድሩ እንዲታገዱ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል። ናቫልኒ እና ደጋፊዎቻቸው ግን፣ "ውሳኔው በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት የተላለፈ ነው" ይላሉ።
አሁን ናቫልኒ "መራጩ ሕዝብ እንዳይሳተፍና ድምፁም እንዳይሰጥ" በማለት ዘመቻ ይጀምራሉ።
የክሬምሊኑ ቤተ መንግሥት አፈ ቀላጤ ዴሚትርይ ፖስኮቭ ደግሞ፣
"ይህ የናቫልኒ አካሄድ ህገ መንግሥታዊ መሆኑ አጠያያቂ ነውና በወጉ ይመርመር" በማለት በዛሬው ዕለት መግለጫ ያወጡት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ