በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔቶ ሩሲያ የኒውክለር ሥምምነቱን እንድታከብር አሳሰበ


FILE - A nuclear-capable Russian Topol M intercontinental ballistic missile with launch vehicle rolls along Red Square during a military parade, in Moscow, Russia, May 9, 2017.
FILE - A nuclear-capable Russian Topol M intercontinental ballistic missile with launch vehicle rolls along Red Square during a military parade, in Moscow, Russia, May 9, 2017.

ኔቶ፣ ሩሲያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የፈረመችውን ቀሪውንና የመጨረሻውን የኒውክለር ቁጥጥር ሥምምነት እያከበረች አለመሆንዋ ያሳሰበው መሆኑን ዛሬ ዓርብ በአባላቱ በኩል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሩሲያውን የዩክሬን ወረራ ተከትሎ ውጥረት እየተባባሰ ባለበት ሰዓት፣ የኔቶ ኃይሎች መሪ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሞስኮ አስርት ዓመታትን ያስቆጠረውን “የኒው ስታርት ፓክት” ወይም የአዲስ ጅማሮ ሥምምነትን አሰመልክቶ የገባቸውን ቃል አልጠበቀችም ስትል ከሳለች።

ባለፈው ማክሰኞ፣ ዋሽንግተን፣ ሩሲያ በሥምምነቱ መሰረት የተገባውን ቁጥጥር እና በጉዳዩ ዙሪያ የሚደረገውን ንግግር መሰረዟን አውግዛለች። ይሁን እንጂ የቀዝቃዛው ጦርነት ባላንጣዋ የኒውክለር ጦር መሳሪያዎችዋን ከተደረሰበት ሥምምነት ውጭ እያስፋፋች ነው ስትል አልከሰሰችም።

“የኔቶ አጋሮች የአዲስ ጅማሮ ሥምምነት የሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስን የኒውክለር ስትራቴጂ ኃይሎች በመገደብ ለዓለም አቀፍ መረጋጋት አስተዋጽ ማድረጉን ይስማማሉ” ሲሉ 30 የህብረቱ ጠንካራ አባላት ባወጡት የጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

“ስለሆነም ሩሲያ በህግ አሳሪ የሆነውን የአዲስ ጅማሮ ሥምምነትን ማክበር አለመቻሏን በስጋት ተገንዝበናል” ያለው የአባላቱ መግለጫ “ሩሲያ ግዴታዎችዋን በመወጣት ተቆጣጣሪዎቹ እንዲመለሱና ንግግሩም እንዲጀመር እንድትፈቅድ ጥሪያችንን እናቀርባለን”ብሏል።

ሩሲያ በበኩሏ ዋሽንግተን በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረውን የመሳሪያ ቁጥጥር ሰርዛለች ስትል ትከሳለች።

ሞስኮ ባላፈው ነሀሴ ወር መግቢያ ላይ፣ የአዲስ ጅማሮ ስምምነትን በመጣስ ዩናይትድ ስቴትስ ተቆጣጣሪዎች የጦር ሰፈሮችዋን እንዳይመረምሩ አዛለች። ለዚህም የሰጠችው ምክንያት ዋሽንግተን በተመሳሳይ መደረግ የነበረበትን የሩሲያ ተቆጣጣሪዎችን አግዳለች በሚል ነው።

ዋሽንግተን የሩሲያን ክስ አስተባብላለች።

XS
SM
MD
LG