በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኔቶ መግለጫ

የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልቴንበርግ
የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልቴንበርግ

ኔቶ /የሰሜን አትላንቲክ የቃልኪዳን ሀገሮች ድርጅት/ በሰጠው መግለጫ፣ የቀድሞውን ሩስያዊ ሰላይና ባለቤታቸውን እንግሊዝ ውስጥ መርዘው ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰባት ሩስያውያንን፣ ከድርጅቱ ተልዕኮ አባልነት እንዳባረረ ይፋ አደረገ።

ኔቶ /የሰሜን አትላንቲክ የቃልኪዳን ሀገሮች ድርጅት/ በሰጠው መግለጫ፣ የቀድሞውን ሩስያዊ ሰላይና ባለቤታቸውን እንግሊዝ ውስጥ መርዘው ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰባት ሩስያውያንን፣ ከድርጅቱ ተልዕኮ አባልነት እንዳባረረ ይፋ አደረገ።

የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልቴንበርግ ዛሬ ማስከኞ በተናገሩ ቃል “ሰባቱ፣ ከድርጅቱ ተባረዋል፣ ሌሎች ሦስት ደግሞ የአባልነት መታወቂያቸው ታግዷል” ማለታቸው ተሰምቷል።

ይህም፣ ሩስያ ላደረገችው ጥፋትና ላሳየችው ያልተገባ ሥነ ሥርዓት ተገቢውን መልዕክት ያተላልፋል ብለን እናምናለን” ሲሉም ዋና ጸሐፊው አክለው ተናግረዋል።

የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት፣ ሩስያ በሚሽኑ ውስጥ የነበራትን ተሳትፎ በ10 በመቀነስ፣ በጠቅላላው ሃያ እንዲሆን እንደተወሰነም ነው ስቶልቴንበርግ ያስታወቁት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG