ዋሺንግተን ዲሲ —
ሩስያ በቅርቡ ዩክሬይን ላይ ባደረገችው ጥቃት የተነሳ፣ የተመድ ሰብሰባ ሊቀመጥ መሆኑ ተሰማ። ሩስያ በዩክሬይን የባሕር ኃይል መርከቦች ላይ ያደረሰችው ጥቃት፣ የድርጅቱ የዚህ ሳምንት ስብሰባ፣ ቀዳሚ አጀንዳው እንደሚሆን ነው የተገለጸው።
የዩናይትድ ስቴትሱ ውጩ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ነገ ማስከኞ ብራስልስ ውስጥ ሊካሄድ በታቀደው ስብሰባ ላይ ከሚገኙት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር እንደሚገናኙም ታውቋል።
ሩስያ ባለፈው ሳምንት በዩክሬይን መርከቦች ላይ ያደረሰችው ጥቃት ወደ ከፋ ጦርነት እንዳይሄድ ያስጠነቀቀች ሲሆን፣ ሞስኮ በበኩሏ ዩክሬንን በጠብ ጫሪነት ከሳለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ