በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ሚሳይል በመተኮስዋ ዓለምቀፍ ዕርምጃ እንዲወስደባት ኔቶ አሳሰበ


ሰሜን ኮሪያ አሁንም ሚሳይል በመተኮስዋ ላይ ዓለምቀፍ ዕርምጃ እንዲወስደባት የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አሳሰበ።

ሰሜን ኮሪያ አሁንም ሚሳይል በመተኮስዋ ላይ ዓለምቀፍ ዕርምጃ እንዲወስደባት የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አሳሰበ።

የኔቶ ዋና ጸኃፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ሰሜን ኮሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔዎችን በማን አለብኝነት በመጣስ ሚሳይል ተኩሳለች። ይህም በዓለምቀፍ ሰላምና ጸጥታ ላይ የተሰነዘረ ከባድ ሥጋት እንደመሆኑ ዓለምቀፍ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል ብለዋል።

ሰሜን ኮሪያ ለሥድስተኛ ጊዜ የኒውክሊየር ሙከራ በማካሄዱዋ ዓለምቀፉ ማኅበረሠብ ተጨማሪ ማዕቀብ ጥሎባታል። ያ ከሆነ ከጥቂት ቀናት በኋላ ትናንት የተከሰችው ሚሳይል በጃፓን ሆካይዶ ደሴት ሰማይ ላይ ማለፉ ተገልጿል።

የጃፓን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዋና ሚንሲትር ዩሲዳ ሱጋ ባወጡት መግለጫ ከሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የሚሰነዘርብንን ትንኮሳ ልንቀበል አንችልም። በመሆኑም የተቃውሞ መልዕክታችን እጅግ ከፍተኛ ከሆነ ቁጣ ጋር እንዲደርሳት እንፈልጋለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG