በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔቶ ከፍተኛ የተባለ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርግ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የኔቶ አርማ
ፎቶ ፋይል፦ የኔቶ አርማ

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በመጪው ሳምንት 90 ሺሕ ወታደሮች የሚሳተፉበትንና ከአሥርት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛው ነው የተባለ የጦር ልምምድ እንደሚያደርግ ታውቋል።

“ስቴድፋስት ዲፌንደር 24” የተሰኘው እና ለወራት የሚቆየው ልምምድ፣ የቃል ኪዳን ድርጅቱ ግዛቶቹን ሁሉ እንደሚከላከል ለሩሲያ ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል። ልምምዱ የሚደረገው የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት አሸናፊ በሌለበት ሁኔታ በመቀጠል ላይ ሣለ ነው።

ፕሬዝደንት ፑቲን በዩክሬን ላይ ጥቃት እንዲጀመር ከማዘዛቸው ቀደም ብሉ ባሉት ወራት፣ ኔቶ በሩሲያና በዩክሬን አካባቢ ባሉ ግዛቶቹ የመከላከያ አቅሙን በማጠናከር ላይ እንደነበር ታውቋል።

ለመካሄድ የታቀደው ልምምድና በአካባቢው ኔቶ የሚያደርግው እንቅስቃሴ ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ የታየ ትልቁ እንቅስቃሴ ነው ተብሏል።

ልምምዱ በተጨማሪም ሩሲያ የኔቶ አባል አገርን ከማጥቃት እንትታቀብ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

እንግሊዝ ለልምምዱ 20 ሺሕ ጦሯን፣ ተዋጊ ጄቶች፣ የቅኝት አውሮፕላኖችን፣ የጦር መርከቦችን እና ባሕር ሰርጓጅ መርከቦችን እንደምክትልክ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG