በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኔቶ አባል ሀገሮች የመከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ በብረሰልስ


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ዛሬ እና ነገ ዐርብ በሚካሄደው የሰሜን አትላንቲክ ሃገሮች ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አባል ሀገሮች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ ብረሰልስ ተጉዘዋል።

በስብሰባው ላይ ስለአፍጋኒስታን የጸጥታ ጉዳዮች፥ ከሩስያ ጋር ስላለው ውጥረት እና ስለቴክኖሎጂ ፖሊሲዎች ውይይት እንደሚያደረግ ተገልጿል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኦስተን ትናንት ረቡዕ ብረሰልስ እንደገቡ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ቃል "የመጣሁት ኔቶ ወታደራዊ ቁመናውን ወደፊት የሚከሰቱ ለሚከሰቱ ፈተናዎች ዝግጁ በሚያደርገው መንገድ እንዲያስተካክል በመግፋት ለማገዝ ነው" ብለዋል።

የኔቶ ዋና ጸኃፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ በበኩላቸው የመከላከያ ሚኒስትሮቹ አፍጋኒስታን የአሸባሪዎች መደበቂያ እንዳትሆን ለመከላከል ስለሚቻልበት መንገድ እንደሚወያዩ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከአፍጋኒስታን በአየር የወጡት ብዛት ያላቸው የሀገሪቱ ዜጎች በመሸጋገሪያ ማዕከሎች ሳይቆዩ የኔቶ አባል ሃገሮች ተቀብለው ማስፈር እንደሚገባቸው ሚንስትሮቹ የሚነጋገሩበት መሆኑን የኔቶ ዋና ጸሃፊው ገልጸዋል።

የእሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ቀደም ብለው ሮሜንያን የጎበኙ ሲሆን በዚያ ባደረጉት ንግግር የባይደን አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስን እና የአውሮፓን አትላንቲክን ተሻጋሪ ትሥሥሮች ለማጠናከር እንዲሁም የኔቶን የምስራቅ አውሮፓ አባል ሃገሮች ጸጥታ ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ማክሰኞ ዩክሬይን ኪየቭ ከተማ ላይ ባደረጉት ንግግር ሩስያ በምስራቅ ዩክሬን ጦርነት በሰላማዊ መንግድ እንዳይገታ ማናቸውንም እንቅፋት ከመደቀን እንድትቆጠብ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG